Tender Detail

Tender Details

  • Company Dagmawi Menelik Comprehensive Specialized Hospital Communication (የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address የካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-123-42 72
  • Websitehttps://hakimethio.org/facility/menelik-ii-referral-hospital/
  • Deadline24 Feb 2024, 11:50 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ዳ/ም/ኮ/ስፔ/ሆ/ል/08/2015

Dagmawi Menelik Comprehensive Specialized Hospital Communication (የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)


የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቪ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሆስፒታል አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ዕቃዎችን ለተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ ቁ

ሎት

የጨረታ ዓይነት

የጨረታ

ማስከበሪያ

ምርመራ

01

ሎት 33

አገልግሎት የማይሰጡ የህክምና ካርዶች እና ጋዜጣዎች ሽያጭ

100,000

 

 

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ -

1 በዘርፉ የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3 የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።

4. የነቢዎች ከሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት ደብዳቤ ያላቸው::

5. በመንግስት ግዥ አቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው

6. በመንግስት ግዥ ያልታገዱ።

7 የጨረታው ማስከበሪያ በCPO ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::

8. የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርጫፎች ብቻ መሆን አለበት፡፡

9. የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 ብር በመከፈል በሆስፒታሉ የከፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር B-008 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 069 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12 ተጫራቾች የሚጫረቻ ሰንዳቸውን የፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየተ በአራት (4) በተለያዩ ፓስታዎች በማሸግ ፊርማና ማህተም ተደርጎ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ሆ/ሉ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ሆ/ሉ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅጽ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል።

13 የጨረታ ሣጥኑ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ በዓል/ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

14 የጨረታ ማስከበሪያ በሎቱ በቀረበው መሰረት ነው።

15 በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሽነፈውን ንበረቶች/ዕቃዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ አለበት።

16 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድመው ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ሆስፒታሉ ኃላፊነት አይወስድም። በጨረትው ተሽጦ የትወሰደ ዕቃ/ንብረት ተመላሽ አይደረግም። ለዕቃው/ንብረቱ የተከፈል ገንዘብም አይመለስም።

17 ተጫራችቾ ሰንድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋት 3፡00 እስከ 10፡00 ሠዓት ዕቃዎቹና/ንብረቶች በሚገኙበት በሆስፒታሉ ውስጥ በመገኘት መመልክት ይችላሉ።

18 አሽናፊው ተጫራች ስለማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ያሽነፈበትን ዕቃ/ንብረት ዋጋ ገቢ አድርጎ መረከብ አለበት በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ገንዘብን ገቢ ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ወይም የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተምለከረለት CPO ያስያዘው ገንዘብ ለሆስፒታሉ ገቢ ይደረጋል።

19 ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጫ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ አ አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ዳግማዊ ምኒልክ ኮፕሪሄንሲቭላይዝድ ሆስፒታል

ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0952545407/011 123 42 72/011 126 02 80 የደውሉ።

ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender