Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Feb 2024, 12:38 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


በፍ/ባለመበት አቶ አህመድ ሰይድ እና በፍ/ባለዕዳ ኮንስታብል ተክሌ ወሰኑ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 134604 በ022/7/2015 ዓ/ም እና በመ/ቁ136094 በ12/10/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ወረዳ በፍርድ ባለዕዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ጅምር መኖሪያ ቤት ቦታ ስፋት 140 ካ.ሜ ላይ የሚገኝ ማህበር ካርታ ቁጥር L/00095/2011 በ06/7/2011 ዓ/ም ፕርስል ልዩ ቁጥር B29-18 የሆነው ቤት የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 243,000 (ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ብር ) ሆኖ የትራንዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቶች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡ 30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ እሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡

በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከእሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender