የጨረታ ማስታወቂያ
ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ ማህበር (ማማ ወተት)
የሰበታ አግሮኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በዋናው ግቢ ደረጃውን የጠበቀና እስከ 120 ሰው የሚይዝ የስብሰባ አዳራሽ ለማስገንባት ይፈልጋል::
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የአዳራሹ ዲዛይን ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዲዛይንና የማቴሪያል ዓይነት የሚወሰን ሆኖ ተገጣጣሚ ቤቶች የሚገነቡትንም ያካትታል!
3. የዲዛይኑ Detail የሚቀርበው በA3 Paper Color Print ሆኖ በሐርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ መቅረብ አለበት፤
4. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ክፍያ የሚፈፀምለት በአራት ዙር ሲሆን የመጀመሪያው ክፍያ 25/100 የጠቅላላ ስራው 30/100 ሲከናወን የሚከፈል ሲሆን ሁለተኛው 25/100 ክፍያ የጠቅላላ ስራው 60/100 ሲጠናቀቅ የሚከፈል ይሆናል:: ሶስተኛው ዙር 25/100 ክፍያ የጠቅላላ ስራው 90/100 ሲጠናቀቅ የሚከፈል ሆኖ የመጨረሻ h९ः१ 20/100 ९११ ८ 100/100 ms & Chith ሲደረግ የሚከፈል ይሆናል አሽናው የጨረታውን 5/100 ለሁለት አመት የሚያዝ (Retention)ማስያዝ ይኖርበታል::
5. የማስረከቢያ ጊዜ አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 90 ቀን ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርበታል፣
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 14 (25/100) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) በሰበታ አግሮኢንዱስተሪ ኃ/የተ/የግ/ማ ስም ማስገባት ወይም ማስያዝ አለባቸው፣
7. ተጫራቾች ለጨረታ ያሲያዙት ገንዘብ የጨረታ ውድድሩ ተጠናቆ አሽናፊው እንደታወቀ ወዲያው ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
8. የጨረታ ማስገቢያ ቦታ የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት አለምገና ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሰበታ መንገድ በሚገኘው ዋናው የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ነው::
9. ተጫራቾች የስብሰባ አዳራሹ የሚያርፍበትን ቦታ በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ!
10.ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናትይቆያል::
11. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣ ከወጣ በ15ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 በስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል :: (15ኛው ቀን እሁድ ላይ ከዋለ/በዓል ከሆነ በተከታዩ ቀን ይሆናል)
12.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ሰበታ አገር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ማማ ወተት)
ስልክ ቁጥር 011 3 38 41 05/011 3 66 20 66/0113380039
አድራሻ - አለምገና ከሚካሌል ቤ/ክርስቲያን ወረድ ብሎ
