Tender Detail

Tender Details

  • Company ሆሣ ትምህርት ኮሌጅ
  • Address , Phone: 0465552651
  • Website
  • Deadline16 Feb 2024, 4:12 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ

ሆሣ ትምህርት ኮሌጅ


የሆሣዕና ትምህርት ኮሌጅ በ2016 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1. አላቂ የትምህርት ጽ/መሣሪያዎች!

ሎት 2 ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች፣

ሎት 3 የደንብ ልብስ፣

ሎት 4 የወንድና የሴት አጭር ቆዳ ጫማ፤

ሎት 5 መኪና ጎማ፣

ሎት 6 የስፖርት ዕቃዎች፤

1. በዘረፉ ወይም በንግድ ሥራ መስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት

ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

5. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።

6. ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የማይመለስ ለእያንዳንዱ 50.00/ሃምሣ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን በሥራ ሰዓት ከሆሣዕና ትም/ኮሌጅ ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስት ለሙወዳደሩበት ሎት 1 እና ሎት 5 ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ ሎት 2,3,4 እና ሎት 6 ለእያንዳንዱ ብር 5,000.00/አምስት ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ይክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አርጅናል እና ኮፒ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ሆሣዕና ትምህርት ኮሌጅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሣዕና ትም/ኮሌጅ አዳራሽ ይከፈታል:፡ የሚከፈተው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

10. ኮሌጁ ስለግዥ አፈጻጸሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል። ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም ይወረሳል፣

12. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0465552651 ወይም 0465552652 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ሆሣዕና ትምህርት ኮሌጅ

Save Tender