ልዩልዩ ያገስገሱ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ASPSC 02/2016
አፋር
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ ወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ፡-
1. የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው የአ/ማሕበሩ አድራሻ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስኪከፈት ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ንብረቶቹ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው በማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ግቢ እንዲሁም
ካፒታል ሆቴል ጀርባ በሚገኘው የአ/ማሕበሩ ዋና መ/ቤት በመምጣት መመልከት ይቻላል::
3. ተጫራቾች ለመግዛት ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች ዋጋ 20% (ሃያ ከመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም::
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው::
7. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሠነዶቻቸው ላይ የተጫራቹን ስም፤ ሙሉ አድራሻቸውንና ስልከ ቁጥራቸውን አስፍረውና ፊርመው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት አይነትና ዋጋ/ከተእታ ጋር/ በቁጥርና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገው ኤንቬሎፕ በአ/ማሕበሩ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
9. ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 011-618 8250 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሻለቃ ኃይሴ ገ/ሥላሴ ጎዳና ከካፒታል ሆቴል ጀርባ
አፋር ጨው ማምረቻ አ/ማሕበር
