ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምቦልቻ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ሲአይፒ በጀት በ2016 በጀት አመት በተያዘው የ Bridge design on meja sheleko in meja kebebel
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፤
3. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ከፋይነት
የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. በመንገድ እና ድልድይ አማካሪ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆነ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን አርጅናል ማስረጃዎች እና ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ ከ04/06/2016 እስከ 24/06/2016 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ CPO /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንከ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 37.500.00 /ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል፡፡
9. የሚሰሩ Bridge design on Brokena river ስራዎች ዝርዝር መግለጫ /TOR/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 25/06/2016 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቶች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ጊዜ የበዓል ቀን፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
11. በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡
12. ሲገጥማችሁ አሰሪው መ/ቤት ጨረታ ካወጣው አካል ከጨረታው መከፈቻ እለት በፊት በስልከ ቁጥር 033- 351-10-42/09-75-42-90-ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
13 መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
ኮምቦልቻ
