የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር-006/2016
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በደ/ዘይት ማሰልጠኛ ተቋሙ እየገነባ ለሚገኘዉ የማስፋፊያ ፕሮጀከት የብረት በርና መስኮት ስራዎችን አስፈላጊ ግብዓቶችን አቅርቦ በኮንትራት የሚሰራለት ይፈልጋል፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታዉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስከር ወረቀት ፧ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ታክስ ከሊራንስ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፡
2. ጨረታዉ በአየር ላይ የሚቆየዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነዱ የሚሸጠው በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-11:00 የማይመለስ 300 ብር አዲስ አበባ በሚገኘዉ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 ግዥና ፋይናንስ ጽ/ቤት በመከፈል ደረሰኝ ይዘው 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 208 የአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
3. ጨረታው በአየር ላይ በዋለ በ21ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሺያል እና ቅድመ መገምገሚያዎቹን /ቴከኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው::
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50,000.00/ሀምሳ ሺህ ብር / በCPO ወይም ባንክ ዋስትና ከቴከኒካል/ህጋዊ ሰነዶች /ኦርጂናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
7. .ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልከ ቁጥር 0118-694931/0116-454139
ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
