ሁስተኛ ዙር የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/አስ/ር/ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ለማስገንባት ላቀደው ለአስተዳደር ህንፃ የባለሞያዎች ሽንት ቤት ግንባታ ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ዝቅተኛ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡
1. ደረጃ 5 GC/B.C እና ከዚያ በላይ የሆነ::
2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የቲን ነምበር/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ ያለው/ላት እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ላት እና የ2016 በጀት አመትን ግብር የከፈሉ/ ለች፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ፣ ቢድ ቦንድ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ችል
8. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፍቃድ በማቅረብ በወረዳው በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል መግዛት የሚችል፡፡
9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴከኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በስም በማሸግ በመፈረም እና በጥቅል በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩን ስልክ
ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት፡፡
11. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
12. ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ታሸጐ በዚያው ዕለት 8፡00 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች የተሟላ ሰነድ ካቀረበ ቢገኝም ባይገኝም ሰነዱ ይከፈታል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ:-0917108500/0917503586/0929241731
አድራሻ – የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ለደ/ቤ/ወ/አስ/ር/ጽ/ቤት
