የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አለም ሞገስ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ክበሬ ለማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/294884 በ14/12/2013 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/274625 በ29/10/2013ዓ/ም በ04/09/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ /ከ/ከተማ በቀድሞው ወረዳ 08 በአሁን ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 360 የሆነው ቤት መኖርያ ቤት አስመልከቶ አቶ አበበ ለማ በኑዛዜ የተላለፈላቸው 13.8 ካ/ሜ ሳይጨምር ፍርድ ያረፈበት የቤቱ ስፋት 105.29 ካ/ሜ ሲሆን አጠቃላይ የቦታው ስፋት 248 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,052,900 (አንድ ሚሊዮን ሃምሳ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር) የትራንዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሽጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱንባለበትቦታድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከጠ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
