ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ADIGRAT UNIVERSITY (ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለ2016 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን የሚያገለግሉ ዕቃዎች እና ግብአቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ መሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል፣
3. ተጫራቹ ቲን ሰርተፊኬት ምዝገባ ማቅረብ የሚችል፣
4. ተጫራቹ የማቅረቢያ መታወቂያ ምዝገባ ያለው መሆኑን ማቅረብ የሚችል፤
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
6. ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ቼከ ወይም ባንክ ጋራንቲ ለእያንዳንዱ ሎት እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡
* ሎት 1. የደንብ ልብስ አቅርቦት፣ የጨረታ ማስከበሪያ 150, 000.00 ብር በሲፒአ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችል፣
* ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች አቅርቦት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00
* ሎት 3. የፈሳሽ ቆሻሻ መጠገን እና መዘርጋት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00
* ሎት 4. የታሸገና ንፅህናውን የጠበቀ ሩዝ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00
* ሎት 5. የተፈለጠ ደረቅ እንጨት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00
* ሎት 6 የሲቪል ምህንድስና መሣሪያ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 150,000.00
* ሎት 7 የታሸገ ትንሹ ውሃ ጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00
* ሎት 8 ኤሌክትሮኒከስ የጨረታ ማስከበሪያ 400,000.00
7. ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ 200,00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል፣
8. ማንኛውም ተጫራች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ አለበት፣
9. ጨረታው ማስታወቂያ ላይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ልከ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣
10. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
* ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 0344452318 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
