የጨረታ ማስታወቂያ ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ
BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)
Bunna Insurance Company (S.C)
ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላትን ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹንና የተሽከርካሪ አካላትን መግዛት ለሚፈልጉ ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ወይንም ቃሊቲ የኩባንያችን ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ::
ማሳሰቢያ
✓ ተጫራቾች ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ቃለቲ ሸዋ ዳቦ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ::
✓ጨረታው የካቲት 09 ቀም 2016 4 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የተገኙ ተጫራች ወይንም ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል::
✓ ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም::
✓ ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ወይም Bunna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም::
✓ ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታ በፊት አመታዊ የተሽከርካሪ ግብር እና ቅጣት ቢኖር በገዥ የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ወጪ ያለ ዕዳ ካለ በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል::
✓ የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ::
✓ አሽናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የሥራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል::
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ
ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት
ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
Tel 911-99-31-15/0114626090 ሪከቨሪ 011-1-26-31-46/011-1-26-28-61
