Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline12 Feb 2024, 1:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ለሁለተኛው ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)


ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለምግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡

ለሁለት ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/የአገለግሎት ግዥ

ሎት 1 የዓሣ አቅርቦት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማJላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።

1 ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2016 ዓ/ም ንግድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2 ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3 ማንኛውም ተጫች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

4 የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፋልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5 ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን ፣ ፊርማቸውንና ማህተም አJልተው ማቅረብ አለባቸው።

6 ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይችልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበጥ

7 ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ለማሽነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።

8 ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ20% በመጨመር ወይም እስከ 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።

9 ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 12/6/2016 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።

10 ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተJላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰንድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኃል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፓዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ/COP/ ለብቻው እና ፋይናንሻያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማሰገባት አለባቸው።

11 የጨረታ ሂደቱ የቴክኒካል ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መሰረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤ (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ኝ ቴክኒካል ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፍ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላል።

12 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

 ለበለጠ መረጃ፡፟ ስልክ ቁጥር 011 5 51 91 00/0115 53 07 67/0115 15 73 37

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender