የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢ ግ ሥ ኮ/ብግጨ/09/2016
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን፤ የጭነት ተሽከርካሪ ከነተሣቢው፤ ስቴሽን ዋገን፤ የሠራተኛ ሰርቪስ (ሚኒባስ)፤የመስክ አፕ(ዳ/ጋቢና) እና ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሠረት ከክምችት (From Stock) ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ፈቃድ ያላሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን እና ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋጋ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰንዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 2% (እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር ድረስ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፓሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
ኮርፓሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
ስልክ 011-470-90-95 ወይም 0114-42-36-08
ፋክስ 0114-42-13-12
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን
