Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline13 Feb 2024, 12:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሞጆ ከተማ ቴሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችን ፍላጎቱ ላላቸው ድርፍቶች /ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ /ድርጅት/ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት ድርጅት ከሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 27 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለምሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ላገለገሉ ዕቃዎች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ (የሚጫረቱበትን ዋጋ) 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታ ሰንዱ የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት አድራሻ የበር መግቢያ ፈቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ጨረታውን አየር ላይ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የተጠቀሱት ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በማካተት በሰም በታሸግ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ያካቲት 13 ቀን 2016 ዓ/ም 5፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት አድራሻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ በዕለቱ የካቲት 13 ቀን 2016 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝር ድልዝ ያለው ሰንድ ተቀባይነት የለውም። መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994/022-111-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

            ኢትዮ ቴሌኮም

          ደቡብ ምስራቅ ሪጅን  

Save Tender