Tender Detail

Tender Details

  • Company ኬና የአካል ጉዳተኞች ልጆች መርጃ ድርጅት
  • Address ምዕራብ አርሲ ዞን ሻሻመኔ ከተማ 01 ቀበሌ, Phone: 0462114369
  • Website
  • Deadline01 Feb 2024, 5:02 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልፅ የሂሳብ ምርመራ ጨረታ ማስትወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2024(2015/2016)

ኬና የአካል ጉዳተኞች ልጆች መርጃ ድርጅት


ኬና ፎር ኪድስ ዊዚ ዲስቢሊቲስ የተባለ የገጎ አድራጎት ለትርፍ ያለተkkመ ድርጅት የፋይናንስ ስራ እንቅስቃሴ ከ January 01/2023 እስከ December 31/2023 ድረስ ያለውን የአንድ አመት ማለትም የ2023 የሂሳብ ዘመን ፋይል አቃፊ ኦዲት በውጪ ኦዲተር (External auditor) ሰነዶችን ኢዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

በመሆኑም ኦዲት አድራጊ ተጫራቾች የምከተሉትን መስፈርቶች የምታJሉ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ከታወጀበት እለት አንስቶ አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

  1. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፈቃድ ያገኝ እና የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
  2. በሀገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራን ለማከናወን የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈለበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የተገበረበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው።
  3. የሲቢል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፌዴራል የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣና ኤጀንሲ ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ስልጣና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ ይሚችል ቢሆን ይመረጣል፡
  4. ከሂሳብ መርማሪ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንድ ከዚህ በፊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ይመረጣል፤ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  5. በሂሳብ ምርመራ ያለውን የስራ ልምድ አደራጅቶ ማቅረብ የሚችል።
  6. የድርጅቱን ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን በስራ ላይ ማሰማራት የሚችል። (የባለሙያዎችን የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት አደራጅቶ የሚያቀርብ) ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ሃላፊነቱን መውሰድ የሚችል።
  7. የስራውን ዝርዝርና ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ግዜ እንዲሁም የአንድ ፋይል አቃፊና ጠ/ዋጋ ከነተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት የሚያቀርብ።
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ሻሸመኔ ከተማ 01 ቀበሌ ከኦዳ ክሊኒክ ፊትለፊት በሚገኘው ቢሮ በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ከላይ የተገለፁትንና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝና በፓስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ።
  9. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን 08፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የስራ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚፈፀም ይሆናል
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462114369/0944669548/ ኬና ፎር ኪድስ ዊዝ ዲሰአብሊቲስ

አድራሽ፡ ምዕራብ አርሲ ዞን ሻሻመኔ ከተማ 01 ቀበሌ

ኬና የአካል ጉዳተኞች ልጆች መርጃ ድርጅት

Save Tender