Tender Detail

Tender Details

  • Company የፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ ሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት
  • Address Kirkos, Addis Ababa, Phone: 0115157818
  • Website
  • Deadline01 Feb 2024, 12:02 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 02/2016 ዓ/ም

የፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ ሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት


በልደታ ክ/ከተማ ትም/ጽ/ቤት በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ ሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት በ2016 ዓመት የሚፈልጋቸውን የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡

ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዢ /የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያJሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው ለመወዳድር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ-ገፅ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በተወዳደሩበት ሎት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በትምህርት ቤቱ ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. የጨረታ አሸናፊ 10 % የጨረታ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕልውት አንስቶ በተከታታይ አስር የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ የሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት በበሮ ቁጥር 7 በመምጣት የጨረታ ሰንዱስን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሮፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፍሬህይወት ቁ 1 አፀደሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 28 ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት የፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ ሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ /የበዓል ቀን /ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥኑን ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩባቸውን ሎት 1 ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ት/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
  9. የዘገየ ጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  10. አሽናፊ ተጫራቾች ያሸነፋአቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፓርት ግዥ ፈፃሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ት/ቤቱ ዕቃዎችን የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፦ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሚክሲኮ የፍሬሕይወት ቁ 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤ

በመክላከያ ኢንጅነሪንግ /ሜቴክ/ገባ ብሎ ሌጆ አልሙኒየም አጠገብ ነው ስልክ ቁጥር ፡ 0115157818 ወይም 0115583860

የፍሬሕይወት ቁ 1 አፀደ ሕፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት

Save Tender