Tender Detail

Tender Details

  • Deadline31 Jan 2024, 12:53 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር Gaso/NCB/03/2016


ገዳ ትራንስፓርት እና ሎጀስቲክስ አማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ጎማዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በJJላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. የተጠየቁ መለዋወጫዎችን ከክምችት ያላችሁ ወይም ከውል በኃላ በሁልተ ወር ውስጥ ከውጪ በማስገባት ማስረከብ የምትችሉ
  3. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንፃ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በስም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ያባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፓስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራች በሚያቀርበት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኃል ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  8. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚይስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም
  10. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንድተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተረጋገጠ ነው

አድራሻ ሰንጋተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛው ፎቅ

                                ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011558-25-19

የገዳ ትራንስፓርት እና ሎጀስቲክስ አ/ማ

Save Tender