የጨረታ ማስታወቂያ
አባ ወልደትንሣኤ ግዛው ቦርድ መር የእናቶችና ሕፃናት በጎ አድራጎት ድርጅት ያገለገሉ አንድ ኒሳን ፓትሮል መኪና እና አንድ የቻይና ስሪት የሞተር ብስክሌት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ዝርዝር መረጃ ያየዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀሞሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም አጠገብ በሚገኘው ጽ/ቤታቸን ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተሽከርካሪዎቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስም ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ጊቢ በመገኘት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት የሚችሉ ሲሆን ጋዜጣው ከወጣ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይዘጋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአንድ ተሽከርካሪ የመግዣ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ሲፒኦ በአባ ውልደትንሣኤ ግዛው የእናቶችና የሕፃናት በጎ አድራጎት ድርጅት ስም ከጨረታ ሰንድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት
- የጨረታ ሰንድ ገቢ የሚደረገው ቦሌ ቡልብላ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ጨረታ በታተመበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቡልብላ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ይህን ጨረታ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነድ ማኘት የሚቻል ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114714079/0114714106/0911225743 በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
ማሳሰቢያ፦ የኒሳን ፓትሮል መኪናው ሻንሲ የተመታ ስለሆነ ጠግኖ መንዳትም ሆነ ስም ማዘዋወር የማይቻልና መኪናው ለመለዋወጫነት ብቻ የሚጠቅም መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።
አባ ወልደትንሣኤ ግዛው ቦርድ መር
የእናቶች የሕፃናት በጎ አድራጎት ድርጅት
