የጨረታ ማስታወቂያ
ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአቅርቦት ግዥ ማከናወን ይፈልጋል።
|
ተ ቁ |
ሎት |
የእቃው (የአገልግሎቱ) አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ቀን |
|
1 |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
60,000.00 |
30 እስከ 45 ቀናት |
|
|
|
|
60,000.00 |
በ30 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችgን ዋና መስሪያ ቤት ባህርዳር ወይም በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tsisat.com ማግኘት ይችላል።
የተጫራቾች መመሪያ፦
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ ያአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ወይም ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ከድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት ባህርዳር ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል(unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰንዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፓስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቀላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሐሴ /2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- ኩባንያው በጨረታ ሰንዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን በጽሑፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት የቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበጥ
- ኩባኛው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ማሳሰቢያ፦ እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።
ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
