Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Feb 2024, 5:31 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የግልጽ ጨረታ ቁጥር ጉ/ሆ 01/2016


በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ከ/መንግሥት በጉራጌ ዞን በአሞር ወረዳ የጉንችሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2016 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተዘረዝሩት kሚ እና አላዊ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለምግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

  1. ሎት 01 የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  2. ሎት 02 የተለያዩ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
  3. ሎት 03 የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣
  4. ሎት 04 የተለያዩ ሕትመቶች፣

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፦

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃደ ያላችሁ እና የዘመኑ ግብር መክፈል ፍቃድ ያሳደሳችሁ።
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የምትችሉ።
  3. በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገብት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 4000.00/አራት ሺህ ብር/ ለሎት 02 ብር 4000.00/ኣርት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ በCPO በጉንችሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስም ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው ዕቃዎች ከሆስፒታሉ ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተዘጋጀ የጨረታ ሰንድ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20/05/2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዢ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 51 መውሰድ ይቻላል።
  7. ተጫራቾች ማሽነፋቸውን ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸንፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰንድ በCPO የውል ማስከበሪያ  በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
  8. ተጫራቾች በጨረታ ማሸነፋቸውን ከተለፀበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ ሆስፒታሉ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
  9. ተጫራቾች ለሎት 03 እና ለሎት 04 ከጨረታ ሰንዱ ጋር ናሙና /ስምፕል/ አያያዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰንዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 20/5/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  11. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ጨረታውን መታዘብ ያሚፈልግ ማንኛውም በአካል በተገኙበት በ20/5/2016 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሸጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሆስፒታል ግዢ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 51 የሚከፈት ይሆናል።
  12. አሸናፊ ተጫራቾች የተጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና/ሳምፕል/ ማቅረብ አለባቸው።
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 0113320514፣ 0113320515 ይደውሉ

ጉንችሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender