Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Jan 2024, 12:48 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አ/አ/ስ/ምጸ/ሙ/ኮ/02/2016


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክትሬ ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ፦

ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን እቃዎች

ሎት 2. የፈርኒቸር እቃዎች

ሎት 3. የደንብ ልብሶች፣ የስፓርት ግባዓቶች እና ጫማዎች

ሎት 4. የማስታወቂያ ስፓርት ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያJሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ።

  1. አግባብነት ያለው የታደስ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫሮች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2. ብር 20000.00 (ሃያሺህ ብር)፣ ለሎት 3 ብር 10000.00 (አስር ሺህ ብር) ፣ ለሎት 4 ብር 20000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲ ፒ ኦ /CPO/ ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች በአማርኛ kንk የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ11 ተከተታይ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጲያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር በአ/አ/ሰነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሺን አካውንት ቁጥር 1000540125183 በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኘ በመያዝ የጨረታ ሰንዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሸን በፋይናንስ ዳይሬክቶሬት /ፒያሳ ኤሌያና ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ትንሳኤ ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
  6. ጨረታው ይህ ማቅስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11/አስራ አንድ/የስራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኃላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎ ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ሞልተው እና ማኅተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ዶክመንታቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሽያል) ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ በተነገራቸው ቀን ቀርበው ውላቸውን በመፈረም ውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ለመለየት የሚያስችል ስፔስፊኬሽን ወይም በፎቶ የተደገፈ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
  12. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  13. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመበት ቀን አንስቶ በ15 ቀን ውስጥ እቃዎን ያቀርባል።
  14. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  15. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፣
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣ በተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ካይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-126-6187/011-1266172 ደውለው ያነጋግሩ

አድራሻ፦ አራዳ ክፈለ ከተማ ወረዳ 01 ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት ትንሳኤ ሕንፃ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን

የግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

Save Tender