የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ ፌ ዲ ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ኮስሞቲክስ ስፔር ፓርት ምግብና መጠጥ አልባሳት የጽዳት እቃዎች እና ልዩ ልዩ እቃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ እና ስፔርፓርት፣ኮስሞቲክስ ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 11/2016 ዓ/ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡
- በጨረታው ሽያጭ ስራዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰንዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዞው መቅረብ አለባቸው። ለተሽከርካሪ መኪና ግልጽ ጨረታ የተሽከርካሪ አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለምድቡ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ቁርጥራጭ ብረታብረት 200,000 ብር(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በጋራ ሁምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 08/05/2016 |
08/05/2016/3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 08/05/2016 |
08/05/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፦ በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያቤቱ ገቢ ተድርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆንል፤ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካለወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ የወገዳል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገነ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፦ 033559011 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ ፌ ዲ ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
