Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Feb 2024, 4:56 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ


ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተ ቁ

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ቀን

1

ሎት 1

የኤሌክሮ ሜካኒካል እቃዎች

100,000.00

በ90 ቀናት

2

ሎት 2

ክሎሪኔሽን ታንከር

100,000.00

በ60 ቀናት

3

ሎት 3

ሚክሰርና ኮንክሪት ቫይብሬተር

100,000.00

በ60 ቀናት

4

ሎት 4

ቶታል ስቴሽንና ሌብሊንግ መሳሪያዎች

100,000.00

በ60 ቀናት

5

ሎት 5

የሲሚንቶ ማጎጎዝ

100,000.00

እንደ ፕሮጀክቶች ፎላጎት

6

ሎት 6

የማሽነሪ መለዋውጫዋቸ

100,000.00

በ60 ቀናት

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት ባህር ዳር ወይም በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል።

የተጫራቾች መመሪያ ፤

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎ ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኮሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታ። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ወይም ብር 200.00(ሁለት መቶ ) በመክፈል ከድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት ባህር ዳር ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠርዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO  ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፓስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
  7. ይህ ጨርታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሃሴ /2013/ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
  8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  9. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለጸው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ጸንቶ መቆየት አለበት።
  11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ማሳሰቢያ፦ እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ ባሉት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፦ 058 220 48 26/058 320 25 48 በፋክስ ቁጥራችን 058 220 4830 መጠየቅ ይችላሉ።

ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

Save Tender