Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Dec 2023, 3:42 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር፡ AWACH/NCB/G/01/2016/2023 አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ


የኅብረት ሥራ ማህበር የማህበሩ

የ2016 በጀት ዓመት

ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች

ሎት 2 የፈርኒቸር ዕቃዎች

ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ ተጫራቾች፡

1። በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የድጋፍ ደበዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2 በገንዘቡ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3 የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል

4 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል አዋሬ፣ ኤድና አዲስ ሆቴል ፊት ለፊት ገባ ብሎ አጋር ሕንጻ ፤ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

5 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6። የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁና የተጠየቀውን መስፈርት የሚያሞሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤

7 ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃና አገልግሎት ግዢዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል.

8 ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው በሎት 1 የተገለጹትን ዕቃዎች በተመለከተ ናሙና ማሳየት እንዲሁም የተገለጹትን ዕቃዎች በተመለከተ ከያይነቱ አንድ አንድ ናሙና የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው የናሙናዎቹን ዝርዝር በሁለት ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት አስቀድሞ ለማህበሩ የግዥ ሠራተኛ አሰፈርመው ማስረከብና አንዱን ኮፒ መረከብ ይኖርባቸዋል።

9 በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውና ፊርማቸውን እዲሁም የድርጅቱን ማህተም አሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10 በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

11 የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡15 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

12 ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፍቸው እንደተገለጸላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን በጹሁፍ ለማህበሩ ስራ አስፈጻሚ በ5 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ። በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች በ15 ቀናት ውስጥ በማህበሩ ቀርበው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 011 557 9397 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አጋር ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 301

አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃላ/የተ/መሠ/የህብረት ሥራ ማህበር ዋና ቢሮ 

Save Tender