የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ተቆ 005/2016 ዓ/ም
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ሥራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግባቶችንና የሰው ሃይል በማቅረብ፤ በጥቃቅንና አነስተኛ የሆኑ ተመራቂ ማህበራትን ተቆራጮች ማሞላት ያለባቸው መስፈርቶች
|
ተ ቁ |
የሥራው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
ደረጃ |
የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ወረዳ 07 ራስ አንባ አካባቢ የሚሰራ የቱቦ ቀበራ ሥራ |
25,000 ብር |
በጥቃቅንና አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት |
ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት 2፡30 10፡00 ሰዓት |
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ |
ማስታወቂያ ከወጣበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ጀምሮ |
- ተጫራችቶ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ዶክመንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኀል።
- በዘርፉ የ2015/2016 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ያሚችሉ እና ጊዜው ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግሰት ግዥና ንበረት ማስወገድ ኤጀንሲ የትመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው
- ማንኛውም ሥራ ተቆራጭ ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያለው ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የአጭር ምዝገባ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ትከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ቀርበው መግዛት/መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በ8ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 400 ተዘግቶ ከላይ በሰንጠረዡ በተቀመጠው ሰዓት መሰረት በዕለቱ የሚከፈት ይሆናል።
- ማንኝውም ተጫራቾች (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) የማቅረብ ግዴታ አለባቸው የብር መጠኑንም ከላይ በሰንጠርዡ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጅናል ወይም በፋይናንሻል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፓስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል ብቻ ፋይናንሻል ሰንድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ አራት ሰነድ በአንድ እናት ፓስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የሥራ አይነት ስም በመጻፍ አሸጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ እና በሥራ ዝርዝር በሁሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled unit Rate) ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል።
- ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣ በ8ኛው የሥራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጠጫራቾች ከዚህ በፊት ምንም አይነት ውል ያላቆረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ውል ያቆረጡ ተጫራቾች በጨረታው ቢሳተፉም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪይ (instruction to Bidder (TB)እና Bid Data Sheet) እንዲያነቡ ይመከራል።
- ጨረታው ታጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ8ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
