የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር :ECWCT/NCB/SG-85/2016
የኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፓሬሽን ያገለገሉ መሣሪያዎች እና ተሸከሪካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተምዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልክት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመድ የታደስ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰዓት የሀግር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለክቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው። የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ kንk ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ ያባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ -1ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የኢትዮጲያ ኮንስትርክሽን ሥራዎች ኮርፓሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የሚመለከተውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መቡቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የኢትዮጲያ ኮንስትራክሸን ሥራዎች ኮርፓሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ
አድራሻ፦ ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፦ 0118-13-45-27/0118-72-29-47
የኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ኮርፓሬሽን
በግዥ መምሪያ ቢሮ
