የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2016)
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2016)
ድርጅታችን የኢትዮጲያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሞሉ እና ከዚህ በታች የተዘርዘሩትን ሸቀጦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
- በስሚቲ ሩዝ ረጅሙ (CS:ISO 730-18)
- ፈሳሽ የሱፍ ዘይት(CE17:)and labeling CES 73
- ስኮር ICUMSA 45 (SUGAR CANE)
- የመጸዳጃ ቤት ወረቀት (ES 1129:2005)
- ፈሳሽ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና (CES 258:2020)
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- ለውጭ በስመቲ ሩዝ እና ፈሳሽ የሱፍ ዘይት አምራች ወይም አስመጪና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ሸቀጦች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ በመቀረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ታኀሣሥ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ታኀሣሥ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡10 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኃላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 36 92 24 39
የኢትዮጲያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዲስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
