ግልጽ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ሪጅን በሪጅኑ እና በሪጅኑ ስር ለሚገኙ ሾፕ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ለማግኘት ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆኑት ጋር በማዕቀፍ ውል በኮንትራት በመግባት ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በመኪና ኪራይ አገልግሎት ስራ ላይ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጅማ ፈረንጅ አራዳ ዋናው ሪጅን ቢሮ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 208 ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ወይም www.merkato.com,www.extratender.com & afrotender.com የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መረጃ ማግኘትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ጨረታው ጥር 01 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ በዘርፉ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተ እ ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በዘርፍፉ አራት ዓመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 30,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ ፒ ኦ ፤ ባንክ ዋስትና በኢትዮ ቴሌኮም ስም አሠርተው ውይም በጥሬ ገንዘብ ኢትዮ ቴሌኮም ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሠነዱ ግር ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የከፈታል፤
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ብሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 041110275 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ሪጅን
