ድርጅታችን ከዚህ በታች ባሉት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ አንድ (ሎት 1)፦ ከ2016 እስከ 2018 በጀት ዓመት ያለውን የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ የአገለገሉ ግዥ ፤ በጨረታ ሁለት (ሎት 2) Shanigly Forkift (የፎርክሊፋት ጥገና) (በድጋሚ የወጣ) አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው የተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን በድርጅቱ አዲስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 200.00 ከፍለው መግዛት ፋይናንሻል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፓስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንጻ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሪክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው በ16/5/2016 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰንድ (ከላይ የተገለጹ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብቻ) ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንጻ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ሰልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ -ገጽ(www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
