በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ
በፍ/ባለመብት አቶ አሌክሳንድር ኪሮስ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ መዓዛ ሙሉጌታ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክርክር ጉዳያ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/ቁ/183449 በ13/2015 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/186945 በ21/6/2015 ዓ/ም በ3/4/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ በኮዬ ፈጬ ፕሮጀክት 17 ሳይት የቤ/ቁ/456/64 ብሎክ 456 ስፋቱ 109.77 የሆነው ባለሦስት ኮንዶሚኒዬም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ በፌ/ፋ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በሚል CPO የ400,000.75 (አራት መቶ ሺህ) 75/100)4/4 በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። አሁን የሚሸጠው በፍ/ስ/ሥ/ህ/ቁ/ 428(1) መሰረት ነው።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ጨረታ አዳራሻ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታ ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጦቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ በመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።ከ1/4ኛ አስበልጦ ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበጥ የፍ/አፈ/ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ መሕራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈጻጸም ዳይሬቶሬት
