የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 002/2016
የኢትዮጲያ ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ለሰራተኞች የደንብ ልብስ(የወንድና የሴት ሸሚዞች)፤ ያአደጋ መከላከያ የጫማና የቆዳ ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን የሐገር ውስጥ የተጫራቾች ይጋብዛል። እያንዳዱ የጨረታ ተካፋይ የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦች በግልጽ በመረዳት በጨረታ ሰነዶች ላይ እንዲሞላ ማድርግ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረት ሰንዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ለእያንዳዱ የማይመለሰ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጥረ 01/2016 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በተጫራቾች የሚሞሉ ሰነዶች ላይ ቅጾቹን በመሙላ ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የሚጫረቱበትነ ምድብ (ሎት) እንዲሁም ማህተም ማድርግ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን ጥር 01/2016 ዓ/ም በተጠቀሰው ቦታ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች በቴክኒካል የጨረታ ሰነዳቸው አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉ ናቸው።
- ተጫራቾች በቴክኒካል የጨረታ ሰነዳቸው አካተው መቅረብ ያላባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው።
4.1 ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቅድ ያላቸውና ለዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ፣VAT(የተጨማሪ እሴት ታክስ) እና TIN (ግብር ከፋይ ምዝገባ ም/ወረቀት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የኦርጅናል ኮፒ መረጃ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ግብርና ታክስ ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ሲሆን፤ በእርሳስ ተሞልቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- የተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ላይ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ መልኩ መቀመጥ ያለበት ሲሆን ስርዝ ድለዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ የባለስልጣኑ (የድርጅቱ ባለቤት/ተወካይ) ፊርማ የሌለበት ከሆነ ለአቅርቦቱ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ የጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
የገንዘብ መጠን |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ |
30,000.00 |
|
ሎት 2 |
የጫማና የቆዳ ውጤቾች |
20,000.00 |
- ማነኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ከዚህ በታች በተጠቀሰው የብር መጠን መሰረት ገቢዎች ሚኒስቴር ጽ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ CPO አልያም ደግሞ በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ወይም የከፍያ ትእዛዝ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ዝርዝር ውስጥ በተጫራቹ ምርጫ ማስገባት ይኖርበታ።
- መ/ቤቱ የተጫራቾን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መስፈርቶች የጨረታ መመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያካተተ ስለሆነ በሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾች እንዲተገበሩ ያሳስባል፤
- ተጫራቾች ስለ ማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈደም ማርጋገጫ በመስጠት ግዴታ የሚገባበትን ቅጽ በመፈረም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው ፤
ለተጨማሪ ማብራሪያ
- በስልክ ቁጥር 025 411 65 51 ድሬዳዋ ገቢዎች ሚኒስቴር ግዢና ፋይናንስ አስተዳደር በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
በገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
