የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2016 በጀት አመት በዞን አስተዳደር ስር ሊሚገኙ መምሪዎችና ጽ/ቤቶች የሚሆን፤
1ኛ የተለያዩ አይነት የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ በንጥል ዋጋ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሞሉ ተጫራቾችን እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያላቸው፣
- የግብር መክፈያ መልያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (COP) ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/ ማስገባ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸጋ ፓስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግሥት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፣
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰንዱን ከጎፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ያገኛሉ
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጪ እስከ ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ንብረት ክፍል አምጥቶ በጨረታ ሰንዱ መሠረት መሆኑን በጥራት አርጋጋጭ ኮሚቴ አስፈትሾ ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታውውቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆን የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሸጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ የስ.ቁ 09 13 32 97 28 እና 09 25 28 65 94 ይደዉሉ።
በደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን
ፋይናንስ መምሪያ
