Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Feb 2024, 3:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2016


በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሁለት ዓይነት ኬሚካሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ሎት አንድ 1000 ቶን አሉሚንየም ሰልፌት
  2. ሎት ሁለት 1000 ቶን ሰልፈሪክ አሲድ

1 ስለዚህ በዚህ ዘርፍ የተሰማራችሁ ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ያሚችሎ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉና ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘግጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮፓሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ወይም በዋና መስሪያ ቤት ከአዳማ ወደ አሰላ በሚወስደው መንገድ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የሽያጭ ቢሮ የጨረታ ሰነዱን ከላይ የተጠቀሰውን ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

2  ተጫራቾች ከሚያቅርቡት ሰነድ ጋር በዘርፉ ከታደሰ የንግደ ፈቃድ ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚገዛበትን የጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 2 በመቶ ሲፒኦ ሰርተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ። ጨረታው የሚዘጋው በ20ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል

4 ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ማስተባበሪያ ቢሮ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ ባለው ቢሮችን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5 አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ምርቶቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911734266/0911908087/0911840218 ይጠይቁ ።

አመኬፋ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሸን የአዋሽ መልካሳ

ኬሚካል ፋብሪካ

Save Tender