ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቀጥር 09 2016
ቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፓርት ቢሮ በ2016 በጀት አመት ለሚያከናውናቸው ለመንገድ ስራ አገልግሎት የሚወሉ 3 ገልባጭ መኪናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በበጀት ዓመቱ የንግድ ፈቃዳቸው የታደሠ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመደባችሁ መሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ ያእማችሉ፣
- በመስኩ ስራ ላይ ለመስማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሠነድ የያዘ ዶክመንት የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደስ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን።
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው መንድና ትራነስፓርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳሬክተር ቢሮ ቁጥረ 10 የከፈታል።
- 4የጨረታው መከፈቻ ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ዲከፈት ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ አንድ ኦጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንስና የቴክኒክ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ እና በማሸግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል ሠነዱን ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ 50,000.00/አምሳ ሺህ ብር ብቻ በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀ CPO ብቻ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በፓስታ ለብቻው ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ (ጠቅላላ ዋጋ) ስርዝር ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሠነድ ተቀባይነት የለውም። የሚቀርበው ዋጋ ከ15% ቫት ጋር ወይም ከ15 ቫት በፊት ተብሎ በግልድ ተጽፎ መቀመጥ አለበት ይህ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ኮፒውን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- የገልባጭ መኪናዎች መረካከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሆኖ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኃላ ይሆናል።
- ተጫራቾች ገልባጭ መኪናዎቹ በምጋዘን /በስቶክ/ ለመኖራቸው ከመጫረቻ ስንዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አሸናፊ ሆናቸው ሲረጋገጥ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- መ/ቤታቸን የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መርጃ በስልክ ቁጥር፡ 0577752622 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የቤ/ጉ/ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፓርት ቢሮ አሶሳ
