የዕቃ አቅርቦት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱና በፑል አግልግሎት በሚሰጣቸው ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን እና አሰሪያ ሰራንተኛ ጉዳይ ባለስልጣን 2016 በጀት ዓመት ለቢሮ መገልገያ የአሽከሪካሪ ተሽከሪካሪ ብቃት ማረጋገጫ የትራፊክ ኮምፕሌክስ የካሜራ ቅኝት ዝርጋታ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ የኤሌክትሪክስና ተዛማጀ(ተያያዥ) እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም፦
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የዕቃዎች አቅርቦት ግዥ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 220 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጥ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Uncon-ditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሶስቱም ተቀማት በየራሳቸው ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት ።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሠነዳቸውን የእያንዳንዱን ተቆም በመለየት ቴክኒካል ፋይናሻል ሠነዳቸውን በመለየት ማለትም ቴክንኒካል የጨረቻ ሠነዳቸውን በአንድ ፖስታ የቴክኒካል መመዘኛ እንዲሁም የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዳቸውን በአንድ ፖስታ የዋጋ መወዳደሪያ ብሎ ፖስታው ላይ በመጻፍ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው /በተገኙበት በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 001 ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በእያንዳንዱ ተቆም በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካለ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-220-64-27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአብክም ፕላንና ልማት ቢሮ
