የሐራጅ ሽይአጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ቡና ባንክ አ.ማ እና በፍ/ባለእዳ እነ አቶ ግርማ ድለሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳዩ የፌደራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥረ 02391 በ24/8/2015 ዓ.ም እና በመ/ቁ 05395 በ26/10/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱልሉታ ክ/ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ውስጥ የሚገኙት ሴራሚኮች የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 33,900(ሠላሳ ሦስት ሺ ዘጠኝ መቶ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዘገብው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቡና ባንክ አ/ማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሠ/ቁ 1-34064 አ/አ የሆነው የተሽከሪካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር60,000 (ስልሳ ሺ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፈል መሆኑ ታውቆ ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች መዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፊደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጣቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸ ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል።
ከ1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻአፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበተ መሆኑን እንገልጽለን።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
