Tender Detail

Tender Details

  • Deadline30 Dec 2023, 3:17 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


ቁጥር ህ/ጤ/ሳ/ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆ/ግ/ን/አስ/02/2016

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል በ2016 በጀት ዓመት የጽዳት ግብዓቶች ግዥ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃደ አውጥተው ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጽም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች፤

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃዳቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እ.ሴ.ታ(VAT) ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው፤ በ2016 ዓ/ም በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ድረ ገጽ በአቅራቢያነት የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይይ ቀናት ጎ/ዩ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስ ፍይናንስና በጀት ዋና ገንዘብ ቤት ወይም አዲስ አበባ ካዛንችስ ኢንተር ኮንቲኔታል(ኢንተር ቢስትሮ ካፌ) ፊት ልፊት ከሚገኘው ጎ/ዩ ጉዳይ ማስፈጽሚያ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን ብር 70,000.00(ሰባ ሺህ ብር)ከ118 ቀን ያላነስ በሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ወደ ጨረታ ሳጥን የሚገቡ ሰንዶች ሀ/ ተ/ቁ 1 የተጠቀሱትን ቴክኒካል ሰነዶች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ፣የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የገቡበትን ኦሪጅናል ቅጽ ሞልተው ፈርመውና በድርጅቱ ማህተም አረጋግጠው፣ በአንድ ፖስታ፣ ለ/ ዋጋ የተሞላበትን ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ፣ሐ/ዋጋ የተሞላበትን ሰነድ ኮፒ በአንድ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቅን ጅምሮ እስክ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ጎንደር ዩኒቭርስቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት ጎ/ዩ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ይከፈታል ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጎጉልም። የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል። 
  5. የሚሞላው ዋጋ እቃውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ለማቅረብ የማጎጎዣ፤የጉልበት ዋጋና ታክስ ያካተተ መሆን አለበት የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላ ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስ ወጪን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
  6. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ማስረከብ የሚችለው ጎንደር ዩኒቨርሲቲይ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ግቢ ነው።
  7. ተጫራቾች የሚቀርቡበት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ እስከ 90 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት።
  8. መስሪያ ቤቱ የእቃውን ብዛት 20% ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ፣ ውሉ ከተጠናቀቀም በሆላ እስከ 25% ተጨማሪ ውል የመውሰድና የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦0582115186 ደውሎለው መጠየቅ ይቻላል።

የጎንደር ዩኒቭርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል

 

Save Tender