Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Jul 2023, 1:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

ካንጋሮ ፕላስት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ቀደም ሲል ሲገለገልባቸው የነበረውን የፕላስቲክ ጫማዎች እና የጫማ ሶሎች ሞልዶች አልሙኒየም ሞልዶች ብረት እና ዚጋ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪሎ መሸጥ ይፈልጋል።


1.. ተጫራቾች ቦሌ መንገድ በሚገኘው ሱር ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሕንፃ 4ተኛ ፎቅ በዋና መ/ቤታችን ፋይናስ ክፍል ድረስ በመምጣት የጨረታውን መረጃ የዕቃዎጩን ዝርዝር የተጫራች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. ሠነድ የገዙ ተጫራቾች ማስታወቂያውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀን ከቀኑ 8፤00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች ሰነዱ ላይ በተገለጸው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለዕያንዳዱ የዕቃ ምድብ የብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታው በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተገለትድዱትን የጨረታ መገምገሚያ መስፈርቶች የእያንዳዱ የእቃ ዋጋ እና የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ አሟልቶ መገኝት ይኖርባቸዋል።

5. ከላይ በተራ ቁ.4  የተገለፀውን የጨረታ ሠነድ ያላሟላ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6 የሥራ ቀናት ክፍል ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሱር ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ በፋይናስ ክፍል ይከፈታል።

7. የጭረታው አሸናፊ ያሸናፊዎች ዝርዝር ቭበማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈልና ዕቃዎቹን ማንሳት ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪኢያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ወደ ድርጅቱ ገቢ በማድረግ የጨረታቸው አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁር 0911240063 ወይም 0116631533/34 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላል።

ድርጅቱ ጨረታ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender