የአማራ ህንፃ ስርዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ሲሚንቲ ከዳንጎቴ ሙገር ሙገር ታጠቅ እና ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ወዳሉበት ከተሞች ሲሚንቶ ለማጓጓዝ ህጋዊ ከሆኑ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾ።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የትራንስፖርት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት እዲሁም የባለቤነት መታወቂያ ሊብሬያላቸው።
2. የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ በአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊ ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስድ መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመገኘት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ በመውስድ ከጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ሁኔታውን በማንበብ የጨረታ መመሪያው በሚያሴዘው መሰረት ጨረታውን መሙላት አለባቸው።
3. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀ_ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጥበት ቀን እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ስረስ ብቻ ባህርዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ይዘጋል በዚያኑ ቀን 8፤30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ ቀኑ 8፤00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዚያኑ ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆእ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 058 218 0958/0918292107
