የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዋና መስሪያ ቤቱ ልርሚገኘው የኢትዮጵያ አቬሽን ዩንቨርሲቲ የጥገና እድሳት ፕሮጀክት ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዋና መስሪያ ቤቱ ልርሚገኘው የኢትዮጵያ አቬሽን ዩንቨርሲቲ የጥገና እድሳት ፕሮጀክት ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑ የ2015 የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው በዘርፉ ለመሰማራት የታድሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና TINምዝገባ ወረቀት ያላቸው። VAT ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ወይም በህንፃ ግንባታ ደረጃ አንድ ወይም ደረጃ ሁለት ሥራ ተቋራጭ የሆኑ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 /E99/ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር SSNT-7-382 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ /Deposit Slip Copy/ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናሺያል ዋናውን እና ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለኢትዮጵያ መንገድ ስትራቴጂ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሥሪያ ቤት ጊ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9፡00 ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር ፦ +251 115 17 40128/8025
