በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ያገለሉ የተሽከርካሪ መለወዋወጫ ያገለገሉ 6 የመጋዘን ንብረት በሮች 20 የብረት መስኮቶች እና ሌሎችም የሚሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋግል።
በመሆኑ በጨረታው ለመካፈል ለሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. በጨረታው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ማሳተፍ ይቻላሉ።
2. ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር/TIN/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታትይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ቅጥር ግቢ በሚገኘው አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 መግዛት ይቻላሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይየተወዳደሩትን የእቃ ዝርዝር በመግለጽ የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂአይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ እቃውን በአካል በመምልከት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 35 ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዢና ፋይናስ ቡድን ቢሮ ይ ከፈታል።ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፍታል። በመሆኑም በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል። በመሆኑም የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንናውም የጨረታ ሰነድተቀባይነት የለውም።
6. አሽናፊው በውስጥ ማስታወቂአይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እቃውን መውሰድ ይኖርበትል።
7. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስልክ ቁጥር +251 22 211 67 52 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
