Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Jun 2023, 4:32 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ ብረታ ብረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ከታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ማሽንሪዎች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


ተ.ቁ 1/ ሚክሰር ትራንክ

ተ.ቁ 2 / ሃፍ ትሬን ትራክ

ተ.ቁ 3 / ትራክ ማውንትድ ፓፕ

1. በጨረታ ለመስተፍ የሚችሉ አቅራቢዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች  

1.1 ከስራው ጋር አግባብነት ያለው የ2015 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።

1.2 የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ የሆነ

1.3 የግብር ከፋይ መልያ ቁጥር /TIN/ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

1.4 የተፈረመ እና የማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የገባበት ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር በመክፈል ከ 23/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 06/10/2015 ዓ.ም በስራ ሰዓት በዋናው ቢሮ ባምቢስ ምንትዋብ ህንፃ ገባ ብሎ የሚገኝ መስሪያ ቤት ከግዥና አቅርቦት ክፍል መግዛት ይችላሉ።

3. ጨረታው 06/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፤00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በባንክ ጋራንቲ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በታሸገ ፖስታ ከፋይናሺያል እና ቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ውል ተፈራርሞ ክፍያውን በክፈል መኪናዎችን መረከብ አለባቸው።

6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. ተጫራቾች መኪናዎቹን ለማየት ቃሊቲ ውሃ ልማት 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ማየት ይችላሉ።

                                

Save Tender