ኩባኒያችን ዳሎል ኦይል አ.ማ በተለያየ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ ያስመጣቸ የተሽከርካሪ ዘይቶች እና ቅባቶች ማሸጊያዎች የተጎዳ እና ፈሳሽ ያላቸውን የፍሬን የመሪ የሞተር ዘይቶች እና ግሪስ እንዲሁም የተለያዩ ሀይድሮሊክ ዘይቶች እና የእነዚህ ዘይቶች ባዶ ጀሪካኖች በጨረታ አወዳድሮ ለመእሽጥ ይፈልጋል።
1.ማንኛውም በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ተጫራቾች የዘይቶቹን ዝርዝር እና ዓይነት በአዲስ አበባ ከተማ ሲ.ኤ.ም ሲ ጋስት ሞል ጀርባ በሚገኘው የኩባኒያው መጋዘን ከግንቦት 29ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአካል እየቀረቡ መመልከት ይችላሉ።
2. ማንኛም ተጫራች የማይመልስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ከፍሎ ከግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽን ከኩባኛው የፋይናስ እና አክውንታትስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 10 /አስር በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
4.ተጫራቾች አስፈላጊ መስፈርት አሟልተው እስከ ሰኔ 8ቀን 2015 ዓ.ም 6፡30 ሰዓት ድረስ ኤንቨሎፑን አሽገው በኩባኒያው የሎጀስቲክስ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ኩባኒያው የጨረታውን አሸናፊ ማክሰኞ ሰኔ 10ቀን 2015 ዓ.ም ያሳውቃል።
6. ኩባኒያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፦ ቦሌ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ
የስልክ ቁጥር፦ +251116 67 25 02/03/0/+251 966 00 55 44/+251935402643
