የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቤሮ በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋአጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሰሠረት የሚፈለጋቸውን ግብር/ታክስ ግዴታቸውን በሕግ በተቀመጠው የመክፈያ ጌዜ ስላልከፈሉ የግብር/ታክስ ባለ ዕዳ የሆኑትን አቶ ገ/ኪዳን በየነ ገእ/ጌዮርስ የሆነ ለጋራጅ አገልግሎት የሚውል ልዩ ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የሚገኝ የቦታ ስፋት 3068ካ/ሜ የሆነ /ለ4ኛ ጊዜ የወጣ የባለቤትነት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 4,503,119.26 ነው።
2. ስለ ሀብቱ አሻሻጥ መረጃ ከሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በታክስ ዕዳ የተያዙና የተወሰኑ ንብረቶች አስተዳደር ክፍል አፍሬካ ሕብረት ፊት ለፊት አማር ህንፃ 9ኛ ፎቅ ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ /ዋስትና/ ለእያንዳዱን የጨረታ መነሻ ግምት የተሰራላቸው ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ስም ማስያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ሀብቱን የሚገዙበት ዋጋ በግልጽ በማስፈረም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ብሮ ብሎ በመጻፍ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30/ሰላሳ ቀናት/አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 30ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 203 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በ30ኛው ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ31ኛው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠአቱ 3፡30 ሰዓት 2015 ዓ.ም ተጫእአቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎአቸው በተገኙበት በቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ ይከፈታል።
6. አሸናፊው ያስያዘው ከገዥ ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሀብቱን መረከብ አለበጥ
7. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
8. ቢሮእ ስለ ንብረቶች አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፦ +251-011-557-57-98 ወይም +251-011-557-42-14
