በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተወ የተወረሱና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች /ተሽከርካሪዎችን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ሞባይሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳት የተለያዩ ብረታ ብረት የኤሌክትሪክ ገመዶች ቆርቆሮዎች እና ሊአሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባሉት ሁኔታ በግልጽ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።ከዚህ በታች በቅጹ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከዕረቡ 4:00ሰዓት ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልፃለን። የተለያዩ ከደረጃ በታች የሆኑ ብረታብረት ቆርቆሮዎችን ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች የማምረቻና የማቅለጫ ፋብሪካ ያልቹና ቅ/ጽ/ቤታችን በጨረታ በሚሰጣቹ መመሪያ መሰረት አቅልጣቹ ለመጠቀም የምትፈልጉ ባቻ መሆኑን እንገልጻለን።

1.በቅርጫፍ ጽፈት ቤታችን በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳድር የሚፈልጉ ማንኛውም በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ ግብ የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዱጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥንውስጥ ማስገባት የሚኖርባቹ ሲሆን ለሐራጅጨረታ ደሞ ለጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስምዝገብ ይኖርበታል።
2. የሚሸጠው ዕቃ ተሽከርካሪ ከሆነ ማንኛውም ዕድሜው ከ18ዓመት በላይ የሆነ ኢቲዮጵያዊ በተ.ቁ 1 የተገለፁ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም /C.P.O/ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታ ሊሳተፍ ይችላል።
3. ተጫራቾች የግልፀ ጨረታውን ሰነድ ከሀሙስ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሐራጅ ጨረታውን ደግሞ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በነፃ ማግኘት ይችላሉ።
4. በግልፅና በሐራጅ በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች የተሰጡ ዋጋ አምስት በመቶ/5%/ ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ /CPO/በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ለተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ እና ዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለእያንዳዱ ተሽከርካሪ እና ለሚወዳደሩባቸ ዕቃዎች ብር 100,000.00የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ /CPO/ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት
6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት /ስኬጁል/ መሰረት ይችላሉ።
| ተ.ቁ | የቅ/ጽ/ቤቱ | የጨረታው ዓይነት | የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ | የጨረታ የመዝጊያና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት | ሐራጅ | እስከ 28/09/2015 | ግንቦት 29/2015 4፡00 ሰዓት ጀምሮይካሄዳል |
| ግልፅ | እስከ 29/09/2015 | ግንቦት 30/09/2015 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
7. የጨረታው መክፈቻ ቦታ ፦ አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ባሉበት ወይም በታዛቢው ፊት ይከፈታል።
8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት /CPO/ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገእለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃውን በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11። መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ _011 47_ 85 _03