የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1.በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
2. ዩንቨርስቲው የደንብ ልብሱን የሚያቀርብ ሲሆን በወጣው ጨረታ ዝርዝር መሰረት የተቀመጡትን አገልግሎት አሸናፊ ድርጅቱ ደብ ልብስ ስፌት አገልግሎቴን ዩንቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በሚሰጠው ቦታ እና ቀናት ውስጥ ሰፍቶ ማስረከብ የሚችል።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለእትም የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል።
4. ከላይ የተዘረዘሩትን ምስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱ ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ አስተዳደር ህንፃቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ወይም አዲስ አበባ 4ኪሎ ከቅድስተ ማርያም ቤ/ተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚያ ካፌ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 7 ከሚገኘው ቢሮአችን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ተኛው 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6.የጨረታ ፋይናሺያል ዶክመንት እዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በእያንዳዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስም እና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱ በአግባቡ በመሙላት በማሸግ ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ህንፃ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15ቀናት በኋላ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖራባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ህንፃ ቁጥር 10 ይከፈታል ። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታ ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል።
8. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን በተገለፀበት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በሁስላ በኝባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ ይኖርበታል።
