የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የሚውል የተለያዩ የቢሮ ቋሚ መገልገያ ዕቃዎችን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በነሆኑም ከዚህ በታች የተገጹ መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ እዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በጨረታው የሚወዳድሩ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው እና በመንግስት ግዥንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝርውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ ገጹ /webaite/ አትመው ከጨረታ ሰንዱጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በጨረታ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመእዘገቡ እና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያአቸው መሆኑ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሀር የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ብር 240,000.00 /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /cpo/ወይም ለዘጠና ቀን የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሀር በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁትር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትት በእለቱ ማለትም ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም 8፡45 ሰዓት በፋሲሊስት ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01_ 5512400 የውስጥ መስመር 237/262 እንዲሁም በቀጥታ 011_ 5504931 መጠየቅ ይችላሉ።
