Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 May 2023, 12:05 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printed Advertising Materials

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የመልስ መስጫና የውጤት መግለጫ ወረቀት ህትመት እና የፖስታ ህትመት አገልግሎት እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ስካነርና ፕሪንተር ማሽን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


 የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ት/ቢ/ግ/ጨ/-03/15

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተገለጹ

  1. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የመልስ መስጫና የውጤት መግለጫ ወረቀት ህትመት እና የፖስታ ህትመት አገልግሎት
  2. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ስካነርና ፕሪንተር ማሽን/ (በድጋሚ የወጣ)

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  4. በአቅራቢነት የተመዘገበ
  5. ተጫራቾች የግብር ግዴታ መወጣታቸውን እና በመንግሥት ጨረታ መካፈል እንደሚችሉ የሚገልጽ የገቢዎች ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ሰነዱን ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)  ከቢሮው መግዛት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ጨረታ የብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  8. ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ይዘጋል ፤ እንዲሁም በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/ስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ CPOን ጨምሮ ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. የህትመት ተጫራቾች ቢሮው ያቀረበውን የእያንዳንዱን ህትመት ዓይነት ናሙና ማየት አለባቸው።
  • ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ፡- በስልክ ቁጥር 09 13 41 66 35 መጠየቅ ይችላሉ።

ደቡብ ምዕራብ ኢ/ህ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ

Save Tender