በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም
- የሲኖ ትራክ (SO Truck) የኒሳን ዩዲ (Nissan UD) ፣ የፉቶን ዳምፕ ትራክ (Foton Dump Truck) ፤
- ፎርክ ሊፈት (forclift) ፣ የሎደር (Loader) ፣ የኤክስካቫተር (Excavator) ፣ የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) ፣ የዳምፐር(Damper)፤
- የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ (ZNA pick up) ፤ ሪች(Rich) የቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick up) ፤ የፎቶን ፒክ አፕ(Foton pick up)፤
- የፎርላንድ (Forland) ፣ የፋዎ ቤላ(FAW BELLA) ፣ የኦቲንግ (Oting) ፤ የፎቶን ሚኒ ባስ (Foton mini Bus) ፤
- ሙዳን ባስ (Mudan Bus) ፣ ኤፍሲአር (FSR) ፣ ጋርቤጅ ቲፐር(Garbage Tipper) ፣ ካኒባላይዝ (Canibalize)
- እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን (Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ::
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይ መስቀል ወስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ::
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል::
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ቀይ መስቀል ውስጥ በሚገኘው የጥገና ማአከል የበላይአብ ሞተርስ ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ::
በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሞባይል፡- 0966 21 51 83/84
ስልክ፡- 0114 70 97 23
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
