የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ዕቃዎች እና ተዛማጅ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር BHU 07 2015
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም
- የአይሲቲ ዕቃዎች እና ተዛማጅ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ንግድ መስክ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ማለትም ዓመታዊ የሥራ ግብር / የከፈሉበት ክሊራንስ ደብዳቤ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የመረጃ ሰነዶቻቸውን ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ጨረታ ቢያንስ ሶስት ወር የሚቆይ ማስከበሪያ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ስም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- 3. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ጀምሮ እስከ አስራ አምስት ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለየት ታሸጎ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በሚል ተጽፎ በተናጠል ፖስታ በማድረግ በዚህ ማስታወቂያ በተገለጸው ቀን ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥኑ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ንብረት ከፍል ድረስ ገቢ ወይም ኢንስታሌሽን አድርጎ ክፍያውን ይቀበላል።
- ጨረታው በመንግሥት የግዥ መመሪያ ፤ ህግ እና ደንብ መሰረት የሚመራ ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-046 443 01 74 ፋክስ-046 443 03 55/52
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
